አሜሪካ በአልሸባብ ላይ ባካሄደችው የአየር ላይ ጥቃት 6 የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ተገደሉ

መስከረም 4፣2010

አሜሪካ በሶማሊያ ደቡባዊ ክፍል ባካሄደችው ሶስት ጊዜ የአየር ላይ ጥቃት ስድስት የአልሸባብ የሽብር ቡድን ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ፡፡

ተልዕኮው በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስር የሆነው ይህ ጥቃት የአልቃይዳ ተባባሪ በሆኑ አካላት ላይ የተወሰደ  እርምጃ ነው ተብሏል፡፡

በሽብር ቡድኑ ላይ አስተማማኝ ጥቃት ለመፈፀምም በቂ የሆነ የአካባቢ ጥናት ስራ ተሰርቷል መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።