ባለፈው የነሀሴ ወር አዝጋሚ እድገት ያሳየው የቻይና ኢንዱስትሪ ምርቶች እድገት እየተነቃቃ መምጣቱ ተገለፀ

መስከረም 4፣2010

ባለፈው የነሀሴ ወር አዝጋሚ እድገት ያሳየው የቻይና ኢንዱስትሪ ምርቶች እድገት እየተነቃቃ መምጣቱ ተገለፀ፡፡

ባለፈው የነሀሴ ወር በሀገሪቱ የችርቻሮ ንግድና ኢንቨስትመንት መለስተኛ እድገት ያሳዩ ቢሆንም የኢንዱስትሪ ዘርፉ ግን ዘገምተኛ እድገት ነበረው ተብሏል፡፡

ለዚህም የኢንዱስትሪ ምርቶች ፍላጎት መቀነስና ሞቃታማ የአየር ፀባይ ዋነኛ ምክንያቶች እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡

ቻይና በዘንድሮው የፈረንጆቹ አመት የ6 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

የአገሪቱ ኢኮኖሚ በዘንድሮ የአውሮፓውያኑ አመት ያለፉት ስድስት ወራትም የ6 ነጥብ 9 በመቶ እድገት በማስመዝገብ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡