ኬንያ ለመኪና የማቆሚያ አገልግሎት ክፍያ ማስፈፀሚያ ድሮንን ልትጠቀም ነው

መስከረም 05፣2009

ኬንያ ለመኪና የማቆሚያ አገልግሎት ክፍያ ማስፈፀሚያ ሰው አልባ መለስተኛ የበረራ መሳሪያን (ድሮን) ጥቅም ላይ ልታውል ነው፡፡

ቴክኖሎጅን መሰረት ያደረገ የገንዘብ አጠቃቀም ስርዓት ተግባር ላይ በማዋሏ  ኬንያ ከቀዳሚዎቹ አገራት ተርታ እንደተቀመጠች ብሩኪንግ የተባው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማዕከል ተቋም አመልክቷል፡፡

ከዚህ ውስጥ በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚደረገው የግብይት አገልግሎት ስርዓት በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ያደርጋታል፡፡

በኬንያ ቴክኖሎጂ አቀፍ የገንዘብ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት የሆነው ጃምቦ ፔይ የተባለው ኩባንያ ይፋ እንዳደረገው በናይሮቢ ያለውን የመኪና የማቆሚያ አገልግሎት ስርዓት ለመቆጣጠር  ድሮንን ሊጠቀም መሆኑን አስታውቋል፡፡

በማዕካላዊ የናይሮቢ የንግድ ቀጠና 330 ሺህ የሚጠጉ የህዝብና ግል ተሽከርካሪዎች ለከተማዋ የሚያስገቡት የአገልግሎት ክፍያ አናሳ በመሆኑ ቴክኖሎጂውን ጥቅም ላይ በማዋል ውጤታማ አሰራር ጥቅም ላይ እንደሚውል ኩባንያው አመልክቷል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ናይሮቢ አሽከርካሪዎችና የመኪና ማስቆሚያ አገልግሎቱን ከሚቆጣጠሩት ጋር በመመሳጠር በየወሩ 20 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች፡፡

የድሮን ቁጥጥር ስርዓቱ ጥቅም ላይ መዋሉ ተመሳሳይ የማጭበርበር ሂደቶችን በመቆጣጠርና በደረሰኝ ፈንታ "ኢጂጂ" በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ተግባራዊ በማድረግ ችግሩ ለመፍታት መዘየዱን የጃምቦ ፓየ ኩባንያ አመልክቷል፡፡

ናይሮቢ አዲሱን ስርዓት ተግባር ላይ በማዋል ከፓርኪንግ የሚሰበሰበውን ክፍያ በእጥፍ የማሳደግ እቅድ ወጥናለች፡፡

ምንጭ፡‑ ሲጂቲኤን