የኦማን ሞተር ሳይክለኞች በኢትዮጵያ ባለው ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ

መስከረም 09፣2010

የኦማን ዜግነት ያላቸው ሀገር ተሻጋሪ ሞተርሳይክሎች በኢትዮጵያ ባሉ የቱሪዝም መስህቦችና ሰላም መደነቃቸውን ገለፁ፡፡ 

ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ የገቡት ዘጠኝ ሞተር ሳይክለኞች ሲሆኑ ‹‹የኦማን የጋላቢዎች ክለብ›› በሚል የሚታወቅ ማህበር አባል ናቸው ተብሏል፡፡

የሞተር ሳይክለኞቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በሀገሪቱ የእንግዳ አቀባበል ባህል፣ ሰላም እና ታሪካዊ መስህቦች መደነቃቸውን በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ውብ የሀገሪቱ ገጽታዎች በተገቢው መንገድ ለሌላው አለም ሊተዋወቁ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

ሞተር ሳይክለኞቹ በቀን ከ500 እስከ 800 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ጉዞ በማካሄድ በአጠቃላይ 14 ሺህ ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ ተብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ድረስ የሚዘልቀው የሞተረኞቹ ጉዞ 14 ሀገሮችን የሚሸፍን መሆኑ ተመልክቷል፡፡