ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዴንማርኩ አቻቸው ጋር ተወያዩ

መስከረም 10፣2010

በ72 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ለመገኘት ኒውዮርክ የሚገኙት  ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዴንማርኩ አቻቸው ላርስ ራስሙሰን ጋር በሁለትዮሽና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት መጎልበት የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የዴንማርክ ጠቅላይ ሚንስትር ላርስ ራስሙሰን በበኩላቸው በኢኮኖሚ እድገትና በአረንጓዴ ልማት መስክ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖር እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

በተመድ ስብሰባ ላይ ዋነኛ አጀንዳ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው የህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደት ጋር በተያያዘም ከዚህ በፊት የተጀመረው ስራ የበለጠ እንዲጎለብት የአገራቸው ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የውሃና የአካባቢው ጥበቃ እንቅስቃሴ እንደግፋለንም ብለዋል፡፡

ሪፖርተር፤እናትአለም መለሰ ከኒውዮርክ