ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለአሚሶም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መስከረም 12፣2010

ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በሶማሊያ ለአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ሕብረት /አሚሶም/ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ፡፡

ለአሚሶም ወታደሮቻቸውን ያዋጡ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት በኒዮርክ መክረዋል፡፡

አሚሶም ተልዕኮውን ለመወጣት የበጀት እጥረት እያጋጠመው በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠይቀዋል፡፡

የሶማሊያ ብሔራዊ የደህንነት ኃይል አገሩን መጠበቅና ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ መወጣት እስከሚችል ድረስ አሚሶም ተልዕኮውን በተጠናከረ መልኩ እንዲፈፅም ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ኬይሪ በውይይቱ ወቅት በአገሮቹ የተነሱትን ነጥቦች እንደሚጋሩ ገልፀው ለአገራቸውና ለአሚሶም ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን ሪፖርተራችን እናትዓለም መለሰ ዘግባለች፡፡