የደቡብ ሱዳን ልጃገረዶች በአገራቸው በሚፈፀመው ያለዕድሜ ጋብቻ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን ገለፁ

መስከረም 23፣2010

በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ የደቡብ ሱዳን ልጃገረዶች በአገራቸው በሚፈፀመው ያለዕድሜ ጋብቻ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን ገለፁ፡፡

ተማሪዎቹ ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንዲፈፅሙ በቤተሰቦቻቸው እንደሚገደዱ አስታውቀዋል፡፡

ሴት ተማሪዎች ለጋብቻው ፈቃደኛ ካልሆኑ ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እንደማይሰጧቸውም ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ሕፃናት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአገሪቱ በሚፈፀመው ያለዕድሜ ጋብቻ ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ፡፡

ችግሩ ለመቅረፍም ልጆቹን የሚያስተምሩ መምህራን ማሕበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጣ እየሰሩ መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡