የደቡብ አፍሪካ ቆሻሻዎች ወደ ፋሽን አልባሳት እየተቀየሩ ናቸው

መስከረም 23፣2010

አንድ የደቡብ አፍሪካ ስራ ፈጣሪ ወጣት ቆሻሻዎችን ወደ ፋሽን አልባሳት በመቀየር ለገበያ እያቀረበች እንደሆነ ተነገረ፡፡

ቆሻሻዎችን ወደ ተለያዩ ምርቶች ቀይሮ ዳግም ጥቅም ላይ የማዋል ባህል ባልዳበረባት ደቡብ አፍሪካ የምትኖረው የ20 ዓመት ወጣቷ ባሊ ቶምቤላ የፈጠራ አቅሟን በመጠቀም ከፕላስቲክ የተሰሩ አልባሳትን ዲዛይን በማድረግ ትሰራለች፡፡  

ወጣቷ በአውሮፓያኑ አቆጣጠር 2015 ቤተክርስቲያን ታድሜ እያለሁ ማንኛውም የፈጠራ ውጤቶች እንድናመርት ከተነገረ በኋላ ነበር ከፕላስቲክ የተሰራ ልብስ እንድሰራ መነሳሳት የፈጠረብኝ ብላለች ፡፡ 

ከዚም በኋላ በፈጠራ የተሰሩ የአልባሳት ውጤቶችን በተለያዩ ዲዛይኖች እየሰራሁ እገኛል በሚል ተናግራለች፡፡

በየአመቱ ከመቶ ሚሊዮን ቶን በላይ  ቆሻሻ በሚጠራቀምባት ደቡብ አፍሪካ 10 በመቶ የሚሆነው ቆሻሻ  ብቻ ነው ዳግም ተቀይሮ ጥቅም ላይ የሚውለው። ቀሪው ግን በተለያዩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ወይም በየመንገዱ  ይጣላል ተብሏል፡፡   

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን ድረ-ገጽ