የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪዎች በሩዋንዳ ስልጠና እየወሰዱ ነው

መስከረም 24፣2010

የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የሰልጣኞች ስልጠና በሩዋንዳ ጊሻሪ በሚገኘው የፖሊስ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ስልጠና እየወሰዱ ነው᎓᎓

በስልጠናው እየተሳተፉ ያሉ 25 ፖሊስ ኦፊሰሮች ሲሆኑ ከኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ የተውጣጡ ናቸው።

ለአንድ ወር የሚቆየው ስልጠና የተዘጋጀው በምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ሲሆን ይህም የቀጠናው ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አይነተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል᎓᎓

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የፖሊስ ማሰልጠኛው ትምህርት ቤት ሃላፊ ቪያኒ ንሺሚዪማና የሩዋንዳ ብሄራዊ ፖሊስ ለስልጠና ቅድሚያ ይሰጣል᎓᎓ ምክኒያቱም ፖሊሶች የሚያጋጥማቸውን ፈተና የሚፈቱት በስልጠና ነው ብለዋል᎓᎓

የሰላም ማስጠበቅ ተልእኮ በአንድ አገር ብቻ የሚቻል አይደለም ያሉት ኃላፊው ጎረቤት አገራት ያለንን ተሞክሮ በመለዋወጥና ጥንካሬአችንን በማቀናጀት የአካባቢያችንን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል᎓᎓

ስልጠናው የፖሊስ ሃይሎችን ክህሎት እንደሚያሻሽልና የፖሊስ ሃይሉን ተወዳዳሪና ብቃት ያለው ሃይል ለማድረግ የታለመውን ግብ ያሳካል መባሉን ኒውታይምስ ዘግቧል።