ጉግል ያለሰው እገዛ ቪዲዮዎችን የሚቀርጽ ካሜራ ይፋ አደረገ

መስከረም 26፣2010

ጉግል ያለሰው እገዛ በራሱ ጊዜ ወስኖ ቪዲዮችን የሚቀርጽ ካሜራ ይፋ አደረገ።

በዓይነቱ ትንሽ የሆነው ካሜራው ‹‹ጉግል ክሊፕ›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

ካሜራው ያለሰው ንክኪ የተሻሉ ፎቶዎችን ጨምሮ አጭር የቪዲዮ ምስሎችን በራሱ ጊዜ ወስኖ ይቀርፃል ፡፡

መጀመሪያ በአሜሪካ እንደሚሸጥ የተነገረለት ካሜራው፤ መቼ ለገበያ እንደሚቀርብ ግን ጉግል አላሳወቀም፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ