በአፍሪካ የአይሲቲ ቴክኖሎጂ የስራ እድል እየፈጠረ አይደለም ተባለ

መስከረም 26፣2010

በአፍሪካ የአይሲቲ ቴክኖሎጂ የሚፈለገውን ያህል የስራ እድል እየፈጠረ አለመሆኑ ተገለጸ።

በአንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት የሞባይልና የኢንተርኔት ስርጭት እየጨመረ መምጣት የቴሌኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኑክስ ንግድ እንዲጨምር እያደረገው ቢሆንም የሞባይል ኔትዎርኩ በቂ ባለመሆኑ በአይሲቲ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ቀጠሮ የማሰራት ችግር እንዳለ ነው የተገለጸው᎓᎓

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድና ልማት ኮንፈረንስ ላይ የ2017 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሚል በቀረበው አዲስ ሪፖርት ላይ ነው ችግሮቹ  እንዳሉ ነው የተገለጸው᎓᎓

በሪፖርቱ መሰረት ሴኔጋልና ታንዛኒያ ከአፍሪካ ሃገራት ቴሌኮሙኒኬሽንን የተመለከተ 85 ከመቶ የአይሲቲ አገልግሎቶችን ወደ ውጭ በመላክ ግንባር ቀደሞች ናቸው᎓᎓

በዚህም ኢኮኖሚያቸውን በመደጎም ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው᎓᎓

ሪፖርቱ 479 ሺህ ዜጎች በአይሲቲ ዘርፍ ተቀጥረው እያገለገሉ የሚገኙባት ናይጄሪያ ከምእራብ አፍሪካ ሃገራት በአይሲቲ እና በቴሌኮም ዘርፍ ኢኮኖሚያቸው እያደገ ከሚገኙ ሃገራት አንዷ መሆኗን አመልክቷል᎓᎓

ሴራሊዮን የሞባይል ኔትዎርክ በፍጥነት እያደገ የመጣባት ሃገር ስትሆን የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐፕሊክ፣ ኤርትራና ደቡብ ሱዳን የሞባይል አገልግሎት ያላደገባቸው ሃገራት መሆናቸውን በሪፖርቱ መመልከቱን ዘ ሄራልድ ዘግቧል።