ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲመጣ ውይይት እያደረገ ነው

መስከረም 27፣2010 

ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲመጣ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ በአዲስ አበባ፣በካርቱም፣በጁባ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህም መሰረት የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ኢብራሂም ጋንዱር ጋር በመሆን ከቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ኘሬዝዳንት ሬክ ማቻር ጋር በደቡብ አፍሪካ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡

ዶክተር ወርቅነህ በደቡብ አፍሪካ ቆይታቸው ከደቡብ አፍሪካ ምክትል ኘሬዝዳንት ሴሪል ራማፎዛ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜይት ንኳና ማሻባኔ ጋር በሁለትዮሽና በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ዘገባውን ያደረሰን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው፡፡