በዱባይ ፖሊሶች በሌሉበት አገልግሎት መስጠት የሚችል የዓለማችን የመጀመሪያው ፖሊስ ጣቢያ ተከፈተ

መስከረም 28፣2010

በዱባይ ፖሊሶች በሌሉበት አገልግሎት መስጠት የሚችል የዓለማችን የመጀመሪያው ፖሊስ ጣቢያ መከፈቱ ተገለጸ፡፡

ፖሊስ ጣቢያው በሀገሪቱ የጠረፍ አካባቢ የተከፈተ ሲሆን 12ዐ ካሬ ሜትር የሚሸፍንና ሶስት የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ያሉት ነው ተብሏል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያው ከቀኑ በኋላ በጣቢያ የተገጠሙ ስክሪኖችን በመጫን በመስመር ላይ ካለ ፖሊሶች ጋር መነጋገር ይችላሉ ተብሏል፡፡

አገልግሎቱ በ6 ቋንቋዎች የሚሰጥ ሲሆን ነዋሪዎችም የጠፍባቸውን ንብረት፣ ማሳወቅን ጨምሮ የትራፊክ ቅጣትን መክፈልንና 6ዐ አይነት አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሁለት የፖሊስ አባላት በስፍራው ተገኝተው ነዋሪዎችን ስለአጠቃቀሙ እያገዙ ሲሆን በቅርቡ የፖሊስ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ ለነዋሪዎች ብቻ የተተወ ይሆናል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡