ከአካባቢ አየር ሙቀት አማቂ ጋዝን ስቦ የሚያስወግድ ቴክኖሎጂ ስራውን ጀመረ

መስከረም 29፣2010

‹‹ክላይምዎርክ›› የተባለ የስዊዘርላንድ ኩባንያ ሙቀት አማቂ ጋዞችን ከከባቢ አየር መጦ የማስወገድ ስራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በአለም የመጀመሪያው የንግድ ተቋም እንደሆነ የተነገረለት ቴክኖሎጂው ‹‹ካርቦንዳይኦክሳይድ›› የተባለ በካይ ጋዝን ከከባቢ አየር መጦ በማስወገድ የአለም ሙቀት መጠንን ይቀንሳል ተብሏል፡፡

በአለም የመጀመሪያው የንግድ ተቋም እንደሆነ የተነገረለት ቴክኖሎጂው ‹‹ካርቦንዳይኦክሳይድ›› የተባለ በካይ ጋዝን ከከባቢ አየር መጦ በማስወገድ የአለም ሙቀት መጠንን ይቀንሳል ተብሏል፡፡

ኩባንያው በአሁን ወቅት አገልግሎቱን የሚሰጠው አንድ ቶን ሙቀት አማቂ  ጋዝ ሲያስወግድ 600 ዶላር በማስከፈል መሆኑን ገልጿል፡፡

ሆኖም ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ክፍያው ወደ 200 ዶላር እንዲሁም ከረጅም ጊዜ በሃላ ወደ 100 ዶላር ዝቅ ይላል ነው የተባለው፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 ኩባንያው በርካታ መሳሪያዎችን በመትከል በምድራችን ከሚለቀቀው በካይ ጋዝ አንድ በመቶውን ለማስወገድ መወጠኑን ተናግሯል፡፡ 

እቅዱ የተለጠጠ እንደሆነ ቢነገርም የአለም መንግስታት ቁርጠኝነት ከታከለበት ሊተገበር እንደሚችል ኩባንያው ጠቅሷል፡፡

ምንጭ፦ ኢንዲፔንደንት ድረ-ገጽ