ላይቤሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው

መስከረም 30፤2010

ላይቤሪያ ሶስተኛውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ ጀምራለች፡፡

ላይቤሪያ  በአፍሪካ የመጀመሪያዋን የሴት ፕሬዚዳንትና የሰላም የኖቤል ተሸላሚ በሆነችው አለን ጆንሳን   ላፉት አስር አመታት ስትመራ ቆይታለች፡፡

በዚህ ምርጫ ላይ ፕሬዝዳንት አለን ጆንሰን ተሳታፊ እንደማይሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህም ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግርን በማስተላለፍ እንደምሳሌነት ይጠቀሳሉ ነው የተበላው፡፡

ፕሬዚዳንት አለን ጆንሳንን ለመተካት የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች የነበረው ጆርጅ ዊሃ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጆሴፍ ቦአካኢ ለፕሬዚደንታዊ ምርጫው ዋነኛ ተፎካካር መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በሃገሪቷ እየተካሄደ ባለው ምርጫ ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሃገሪቷ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ 20 የሚሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች መቅረባቸው ታውቋል፡፡

ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከረው ጆርጂ ዊሃ በአሁኑ ምርጫ እድል እንደሚቀናው ተናግሯል፡፡

ምንጭ-ቢቢሲ