የዓለማችን የሴት ተማሪዎች ቁጥር በመቶ ሺህዎች ማሽቆልቆሉ ተገለፀ

መስከረም 30 ፤2010

በዓለማችን የሴት ተማሪዎች ቁጥር ባለፉት አስር አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ በከፍተኛ መጠን ማሽቆልቆሉ ተገለፀ፡፡

በአሁኑ ወቅት ከትምህርት ውጭ የሚገኙ ልጃገረዶች ቁጥር ከ130 ነጥብ 3 ሚሊዮን ወደ 130 ነጥብ 9 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ዘ ዋን ካምፔን የተሰኘው ድርጅት በ122 አገራት በሰራው ጥናት አረጋግጧል፡፡

በጥናቱ ውጤት መሰረት በአለማችን በትምህርት ቤቶች ዝቅተኛውን የሴቶች ቁጥር ያስመዘገቡት እንደ ደቡብ ሱዳን፣ መካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ እና ኒጀር ያሉ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚገኙ አገራት ናቸው፡፡

ነፃነቷን ባገኘች ማግስት ወደ እርስ በርስ ጦርነት ያመራችው ደቡብ ሱዳን 73 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ለትምርት የደረሱ ልጃገረድ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አልታደሉም፡፡

በኒጀር የሚገኙ ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጃገረዶች መካከል 76 በመቶዎቹ እንደሚያገቡ ተገልጿል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ደግሞ ለ80 ተማሪዎች 1 መምህር ብቻ መኖሩም በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

ልጃገረዶች እንዳይማሩ በማድረግ በ4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አፍጋኒስታን ታሊባን የተሰኘው ቡድን ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ በኃይል በመከልከሉ ቁጥራቸው ማሽቆልቆሉ ተገልጿል፡፡

በአገራቱ ባለው የእርስበርስ ጦርነት፣ አለመረጋጋት፣ የከፋ ድህነት እንዲሁም በአንዳንድ አገራት ደግሞ ሴቶችን ወደ ትምህርት ይልቅ ወደ ትዳር በማዘንበላቸው ምክንያት የሴቶቹ ቁጥር ሊያሽቆለቁል መቻሉ ተገልጿል፡፡  

ምንጭ፡- ኢንዲፔንደት