በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ በሺዎች የሚቆጠሩትን ከቤት ንብረታቸው አፈናቀለ

መስከረም 30፤2010

በአሜሪካ ሰሜናዊ ካሊፎርኒያ ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ ተከስቶ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የከፋ ጉዳት አደረሰ፡፡

በአደጋውም በትንሹ የ10 ሰው ህይወት ሲያልፍ የ1ሺህ 500 ዜጎች ንብረት እንደወደመ ተነግሯል፡፡

በወይን ምርት ታዋቂ እንደሆነ በሚነገረው በዚህ ግዛት ባሉ ቦታዎች 20 ሺህ ሰዎች ደግሞ አካባቢያቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ተገደዋል፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት ንፋስ የቀላቀለ ደረቃማ አየር ንበረት እሳቱ በፍጥነት እንዲዛመት ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡

የምድራችን የአየር ንብረት ለውጥ አደጋን ለመከላከል የአለም ሀገራት ከተስማሙበት የፓሪስ አለም አቀፍ የአየር ንብረት ስምምነት የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸውን ከስምምነቱ ማስወጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም ከሀገሪቱ የዴሞክራት ፓርቲ አባላት ብሎም ከአብዛኛው የአለም ሀገራት ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ እና ሲኤንኤን