ራይላ አዲንጋ ዳግም ከሚካሄደው የኬንያ ምርጫ እራሳቸውን አገለሉ

መስከረም 30፤2010

የኬንያው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ አዲንጋ በመጪው ጥቅምት ከሚካሄደው የኬንያ ዳግም ምርጫ እራሳቸውን ማግላቸውን ገለጹ፡፡

የኦዲንጋ ከምርጫው መውጣት ለምርጫ ኮሚሽኑ በተፈለገው ሁኔታ ሪፎርም እንዲያደርግ በቂ ጊዜ ይሰጣል ነው ያሉት፡፡

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን እ.አ.አ በነሃሴ 8 2017 በተደረገው ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታን አሸናፊ ቢያደርግም የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫውን ውጤት ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሪያላ ኦዲንጋ እዚህ ውሳኔ ላይ ይድረሱ እንጂ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ምርጫው በታቀደለት ጊዜ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ/ሮይተርስ