ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን የተባለውን ባቡር ለመሞከር ተዘጋጅታለች

ጥቅምት 1፤2010

የሞሮኮ ኢንጂነሮች በአፍሪካ የመጀመሪያው ፈጣን የተባለውን ባቡር ለመሞከር መዘጋጀታቸው ተገለጸ᎓᎓

በዚህ ሳምንት ይሞከራል የተባለው ፈጣኑ ባቡሩ በሰአት 320 ኪሎ ሜትር እንደሚጓዝ የአገሪቱ የባቡር ቢሮ ገልጿል᎓᎓

አንድ ባቡር በሰአት 275 ኪሎ ሜትር እየተጓዘ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክልል በሚገኙ ኬኒትራ እና ታንጂርስ ከተሞች መድረሱ ተመልክቷል᎓᎓

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጂን ይቪስ ሊ ድሪያን  እንደገለጹት ባቡሩ ከአፍሪካ አህጉር በፍጥነቱ ቀዳሚ ነው ብለዋል᎓᎓

ይህ የባቡር መንገድ  የፈረንሳይና የሞሮኮን ግንኙነት እንደሚያጠናክር  ነው  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተናገሩት᎓᎓

የባቡር ፕሮጀክቱ ወጪ 50 ከመቶው ማለትም 2.4 ቢሊዮን ዶላር የተሸነፈው በፈረንሳይ መንግስት መሆኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።