እሥራኤል ሩሲያ መረጃ የምጠልፍበትን ሶፍትዌር ማግኘቷን አስታወቀች

ጥቅምት 1፤2010

የሩሲያ መንግሥት መረጃ የሚጠልፍበትን ካስፐርስክይ የተባለ ሶፍትዌር ማግኘቷን እሥራኤል አስታወቀች፡፡

የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሩን የአሜሪካ ድርጅቶችን ጨምሮ በዓለም ላይ 4ዐዐ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች እንደሚጠቀሙበት ይፋ ሆኗል፡፡

ከሁለት አመት በላይ ካስፐርስክይ በተሰኘ ኔትወርክ መረጃቸው ሲጠለፍ የቆየው የእሥራኤል ባለሥልጣናት አሜሪካ ከሩሲያ ጣልቃ ገብነት ራሷን እንድትጠብቅ አስጠንቅቀው ነበር ተብሏል፡፡

ይህንም ተከትሎ አሜሪካ ካስፐርስክይ የተሰኘውን የሩሲያ መረጃ ጠላፊ ሶፍትዌር ከመንግሥት ተቋማት ኮምፒዩተሮች ላይ እንዲወገዱ አድርጋለች፡፡

የካስፐርስክይ ቃል አቀባይ ድርጊቱን በእውነታ ላይ ያልተመሠረተ ብለውታል፡፡

ቃል አቀባዩ ካስፐርስክይ የግል ኩባንያ እንደመሆኑ ሩሲያን ጨምሮ ከማንኛውም መንግሥት ጋር ያልተገባ ግንኙነት የለውም ብለዋል፡፡

የአሜሪካ የመረጃ ደህንነቶች የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መረጃ እንዲጠለፍ በማድረግ ባለፈው አመት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት እንዲገቡ አድርገዋል በማለት ሩሲያን ወንጅለዋል፡፡

ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡