የፍልስጤሙ ሀማስ እና ፋታህ ከስምምነት ደረሱ

ጥቅምት 2፤2010

የፍልስጤሙ  ሀማስ እና ፋታህ በካይሮ ባደረጉት ውይይት ከስምምንት መድረሳቸው ተገለፀ፡፡

ሀማስ እና ፋታህ  ለአመታት በመካከላቸው የነበረውን ፀብ ለማቆም ከስምምነት መድረሳቸውን ሃማስ ይፋ አድርጓል፡፡

ጋዛን የሚቆጣጠረው ሀማስ የስምምነቱን ዝርዝር በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ የገለፀ ሲሆን ፋታህ ግን ምንም አስተያየት አለመስጠቱ ተገልጿል፡፡

በካይሮ የተካሄደውን የሁለቱንም ቡድኖች ውይይት ከስምምነት እንዲደርሱ ግብጽ የማሸማገል ስራ  ሰርታለች ተብሏል፡፡

ከስምምነቱ በኋላም የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ራሚ ሃምዳላህ ያልተጠበቀ ጉብኝት በጋዛ አካሂደዋል፡፡

የጋዛን አስተዳደራዊና የጸጥታ ጉዳዮን በባለቤትነት መያዝ የፍልስጤም መንግስት አስተዳደር ሃላፊነት መሆኑን ሃማስ ተናግሯል፡፡

ምንጭ-ቢቢሲ