አሜሪካ ከዩኔስኮ አባልነት እራሷን አገለለች

ጥቅምት 2፤2010

አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፤ ሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ አባልነት በተለያዩ ምክንያቶች እራሷን ማግለሏን አስታወቀች፡፡

እዚህ ውሳኔ ለመድረስ የድርጅቱ ወጪ ከፍተኛ መሆን፤ በእስራኤል ላይ የሚከተለው የተዛባ አካሄድና መዋቅራዊ ክለሳ የሚያስፈልገው ስለመሆኑ እንደ ዋንኛ ምክንያት ሆኖኛል ብላለች አሜሪካ፡፡

ባለፈው አመት ዩኔስኮ ፍልስጤም ሙሉ አባል እንድትሆን እና የአል ሃራም አል ሻሪም እምነት ስፍራ በፍልስጤማውያን ባለቤትነት ስም እንዲመዘገብ መወሰኑ አሜሪካ ታውሞዋን እንድታሰማ አድርጓል፡፡

የዩኔስኮ ዋና ሃላፊ ኢሪና ቦኮቫ በበኩላቸው የአሜሪካ ከድርጅቱ አባልነት መውጣት እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡

የድርጅቱን ስራ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው መደረጉ እጅጉን ጫና እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆነውም በፈረንጆቹ ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሆነና እስከዚያው ድረስ ግን ሙሉ አባልነቷ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡

ከተባለው ጊዜ በኋላ ግን በዩኔስኮ የሚኖራት ድርሻ የታዛቢነት ሚና ብቻ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

ምንጭ ፡ቢቢሲ