ምክር ቤቱ ስምንት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ

ጥቅምት 2፤2010

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሶስተኛ አመት የስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ስምንት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ፡፡

በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንዲታዩ የተመሩት ረቂቅ አዋጆችም የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣የከተማ ፕላን ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ፣የኢንዱስትሪ ኬሚካሎች ምዝገባና አስተዳደር ለመደንገግ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ፣የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ማቋቋሚያ ቻርተርን ለማሻሻል የቀረበ የማሻሻያ ሀሳብ፣የማሪታይም አሰሪና ሠራተኛ ኮንቬንሽንን ለማፅደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የባህር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ዓለም አቀፍ ቲንክታንክ መመሥረቻ ባለ ብዙ ወገን ስምምነትን ለማፅደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፣የአፍሪካ ሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ስምምነት የአፍሪካ ሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል መግለጫ እና የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በሌላ በኩል የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች አመራርና አባላት ምደባን ለመወሰን የቀረበው የውሣኔ ሀሳብ በአባላቱ ውይይት ተደርጎበት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በበላይ ሀድጉ