የጥጥ ምርትን ማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ሰነድ ተዘጋጀ

ጥቅምት 03፣2010

በሀገር ውስጥ የሚመረተውን የጥጥ ምርት ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ሰነድ መዘጋጀቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር መብራህቱ መለሰ ስትራቴጅክ ሰነዱ የጥጥ ልማት አመራረት ሥርዓትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ሰነዱ በሚመለከታቸው አካላት ይሁንታ ካገኘ በኋላ በተያዘው አመት ወደ ትግበራ እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ አንድ ቢሊዬን ደላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት መታቀዱ ይታወሳል ሲል ሪፖርተራችን ተመስገን ሽፈራው ዘግቧል፡፡