የድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ

ጥቅምት 3 ፤2010

የድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን የቀብር ሥነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።

ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቲያትር ቤት ሰርታለች

በ1950ዎቹ መጀመሪያ የፓሊስ ሠራዊት ትያትርና የሙዚቃ ክፍል እራሱን በአዲስ መልክ ሲያደራጅ ከቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት ወደ ክፍሉ እንድትመጣ ተደረገች፤ በይፋም የመጀመሪያዋ የፓሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ ሴት ድምጻዊ በመሆን ክፍሉን ተቀላቀለች ዘመኑም 1952 ዓ.ም ነበር ።

ዘሪቱ ወርቃማ የሙዚቃ ህይወቷን በይበልጥ ያሳለፈችው ከፓሊስ ሠራዊት የሙዚቃና  የቲያትር ክፍል ጋር በቆየችበት ዘመን ነበር። በክፍሉ ቆይታዋም እጅግ በርካታ ዜማዎችን ከኦርኬስትራው ጋር በመሆን አቀንቅናለች።

እንቁጣጣሽ፣ ትዝታን በፓስት እንዲሁም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከብዙዎቹ አይረሴ ሥራዎቿ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ዘሪቱ የአንድ ሴት ልጅ እናት ነበረች።

በጌጡ ተመስገን