የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይናዊያን ቱሪስቶች ቀልብ ለመሳብ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

ጥቅምት 7፣2010

በአለም ላይ ትልቁን የቱሪስቶች ገበያ ቁጥር የያዘውን የቻይናዊያን ቱሪስቶች ቀልብ ለመሳብ እየሰራ መሆኑን  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለፀ።

የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ከአውሮፓውያኑ 1973 ጀምሮ  ቻይናን መዳረሻ ደረገው አየር መንገዱ  በአሁን ሰአት 5 መዳረሻዎች እና በሳምንትም 31 በረራዎች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡

የቻይና _አፍሪካ ቻይና _ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በንግድ ኢንቨስትመንትና   ቱሪዝም እያደገ መሆኑን ገልጸው ቻይናውያን ቱሪስቶች ለመሳብ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በቻይና እና አፍሪካ መካከል   በሚደረጉ    በረራዎች ትልቁን ድርሻ የያዘ  መሆኑን የገለጹት አቶ ተወልደ በቻይና በሚያደርገው በረራ  ለበርካታ  ቻይናውያን በበረራ አስተናጋጅነት የስራ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡

አየር መንገዱ በአሁን ሰአት ወደ ቤጂንግ፣ ቼንገዱ፣ ሸንጋይ፣ ሆንግ ኮንግና ጓዋንግዝሆ እንደሚበር የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም በሼንዝኄን በረራ ለመጀመር አቅዷል፡፡

ምንጭ-ሺንዋ