ኮንጎ ለተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባልነት ተመረጠች

ጥቅምት 7፣2010

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 15 ሀገራት አባል ለሆኑበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባልነት ተመረጠች፡፡

የዲሞክራቲክ ኮንጎ መመረጥ ከአፍሪካ የተወከሉ ሀገራትን ቁጥር 4 አድርሷል፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎ መመረጧን ተከትሎ አሜሪካ እና ብሪታኒያ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ሲጅቲኤን ዘግቧል፡፡

የሀገራቱ የተቃውሞው ምንጭ ደግሞ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ ያለውን ሰብዓዊ መብት ሳታስጠብቅ እንዴት ለዓለም ሰብዓዊ መብት ትቆማለች የሚል ነው፡፡

ትናንት በተካሄደው ምርጫ ናይጀሪያ እና ኳታር ዳግም ተመርጠዋል፡፡