አብላጫ የምርጫ ሥርዓት በቅይጥ ትይዩ ምርጫ ሥርዓት እንዲሻሻል የፖለቲካ ፓርቲዎች ተስማሙ

ጥቅምት 7፣2010

አብላጫ የምርጫ ሥርዓት በቅይጥ ትይዩ ምርጫ ሥርዓት እንዲሻሻል ኢህአዴግ ባቀረበው የአማራጭ ሀሳብ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተስማሙ፡፡

ኢራፓ በበኩሉ በአማራጭ ሀሳቡ ላይ እንደማይስማማ አስታውቋል፡፡

ፓርቲዎቹ የአብላጫውና ተመጣጣኝ ድርሻው በመቶኛ ምን ያህል ይሁን በሚለው የክርክር ሀሳብ ላይ መቋጫ ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡