ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ

ጥቅምት 7፣2010

መንግሥት በቅርቡ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ አንዳንድ የንግዱ ማሕበረሰብ አካላት ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡

ባለሥልጣኑ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው የወጭ ምንዛሬ ተመኑ የተደረገው የወጪ ንግድን ለማበረታታት ነው፡፡

ይሁንና ከዚህ ቀደም ወደ ሀገር ውስጥ የገቡትን ምርቶች በመሰወርና በሕገወጥ መልኩ በማከማቸት ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር የሚሰሩ ግለሰቦች ታይተዋል፡፡

በመሆኑም ይህን ድርጊት የሚፈፅሙ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ከዚህ ድርጊታቸው ይታቀቡ ብሏል ባለሥልጣኑ፡፡

ይህን በማያከብሩት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል፡