በኢትዮጵያ የሚመረተው ጤፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነቱ ጨምሯል

ጥቅምት 08፣2010

በኢትዮጵያ የሚመረተው ጤፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ጤፍ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ሰብሎች በግንባር ቀደምትነት  የሚመረጥ ምርት ነው᎓᎓

የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የኤክስቴሽን ፕሮግራም ኃላፊ አቶኢሳያስ ለማ እንደገለጹት ጤፍ የኢትዮጵያውያን የጥንት ሰብል ነው᎓᎓ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውም በኢትዮጵያውያን ገበሬዎች መሆኑን ነው የሚገልፁት᎓᎓

ለ3ሺህ አመታትም በገበሬዎች ሲመረት የነበረ ሰብል መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ፣ልክ እንደ ቡና ሁሉ ጤፍንም ኢትዮጵያ ለአለም ያበረከተችው ምርጥ ሰብል ነው ብለዋል᎓᎓

በኢትዮጵያ ደረጃ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ገበሬዎች በየአመቱ 44ሚሊዮን ኩንታል ጤፍ እንደሚያርቱ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል᎓᎓

በአለፉት አምስት አመታት ምርጥ ዘሮችን እና ዘመናዊ የግብርና  ቴክኖሎጂን በመጠቀም የጤፍ ምርት 40 ከመቶ ጭማሪ እንዳሳየም ተመልክቷል᎓᎓

በኤርትራ፣ በደቡብ አፍሪካ በአሜሪካ በአውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ኔዘርላንድ፣ ስፔንና ህንድ ጤፍ እየተመረተ ለምግብነት እንደሚቀርብ ተረጋግጧል᎓᎓በአለማችን የሚገኘውንና  90 ከመቶ የሚሆነውን ጤፍ  ኢትዮጵያ እንደምታመርትም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በኢትዮጵያ የተፈጥሮ የጤፍ ዝርያ ያለው የብረት ማዕድንና ሌሎች ተያያዥ  ንጥረ ነገሮች የበለፀገ በመሆኑ ጤፍ በሌሎች አገሮች ዘንድ ተፈላጊነቱ እያደገ መምጣቱን ደይሊ ሰባህ የተሰኘው ድረ ገፅ ዘግቧል፡፡