ቻይና የአለም መሪ የምትሆንበት ሁነኛው ወቅት አሁን መሆኑን ፕ/ት ሺ ዥንፒንግ ገለፁ

ጥቅምት 08፣2010

ቻይና  የአለም የመሪነት ሚናዋን የምትቆናጠጥበት ሁነኛው ወቅት አሁን መሆኑን  ፕሬዝዳንት ሺ ዥንፒንግ ገለፁ፡፡

በስልጣን ላይ ያለው የቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ እስከ ፊታችን ማክሰኞ የሚዘልቀውን  ጠቅላላ ጉባኤውን በዝግ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ፕሬዝዳንቱ  ለሶስስ ሰዓታት በዘለቀው የመክፈቻ ንግግራቸው ቻይና አለምን መምራት በሚገባት  አድስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችው ፈጣን እድገትም ለሌሎች አገራት አዲስ የእድገት አመራጭነት ፈር የቀደደ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ   ለውጭ ኢንቨስትመንት  ምቹ  የሆነ የገበያ ሁኔታን ለመፍጠር ፣  የአገልግሎት  ዘርፉን ተደራሽነት ለማስፋፋት ፣  የመገበያያ ገንዘብ እና የፋይናንስ ስርዓቱ ላይ ገበያ ተኮር ለውጦችን ለማስፋፋት እና በተመሳሳይ መልኩ የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት ድርጅቶችን ማጠናከር ላይ  እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል፡፡

በዝግ በሚመክረው የፓርቲው ጉባኤ የአገሪቱን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑትን የማዕከላዊ ፖሊት ቢሮ አባላት ምርጫ ያካዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ ዥንፒንግ በቀጣይም የፓርቲቸያው መሪ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ስብሰባ ላይ የ91 አመቱ  የቀድሞ የቻይና ፕሬዝዳንት ዥያንግ ዜሚንን ጨምሮ ከ2000 በላይ ልዑካን መታደማቸው ተገልጿል፡፡

የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ጉባኤውን የሚያካሂደው በየአምስት አመቱ ነው፡፡

 ምንጭ፡- ቢቢሲና ሮይተርስ