በሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሕፃናት ትኩረት ማግኘት እንዳለባቸው ተገለፀ

ጥቅምት 8 ፤2010

የሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ሕፃናትን ማዕከል ያደረጉ መሆን እንደሚገባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለፁ፡፡

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሕፃናትን ይዘው በጎዳና ላይ ያሉ ሴቶችን ወደ ቤተሰብ ለመመለስ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የስድስት ወራት አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡