የመገናኛ ብዙሀንን ሚና ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ

  ጥቅምት 10፤2010

መንግስት የመገናኛ ብዙሀንን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሻሻል እየሠራ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ገለፁ፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ እና ጤና ነክ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ለማድረግ በኪነ-ጥበብ እና የህትመት ስራዎች ወደ ህብርተሰቡ ሲደርስ የቆየው ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ የተመሰረተበትን 18ኛ አመት አክብሯል፡፡