ብአዴን ከአማራ ክልል ውጪ ከሚሰሩ አመራሮቹ ጋር የሚያካሄደውን ጉባኤ ጀመረ

ጥቅምት 11፣2010

ብአዴን ከአማራ ክልል ውጪ ከሚሰሩ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮቹ ጋር የሚያካሄደውን ጉባኤ ጀመረ፡፡

ጉባኤው ያለፈውን ዓመት የጥልቅ ተሃድሶ አፈፃፀም የሚገምግም ነው፡፡

በዚህ ዓመት የእቅድ አተገባበሮች ላይም መመሪያ ይሰጥበታል ተብሏል፡፡

ጉባኤውን የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ሲመሩት ከየክልሉ የመጡ፣በፌዴራል እና በዲሞክራሲ ተቋማት የሚሰሩ 1ሺ የሚጠጉ አመራሮች ይሳትፉበታል፡፡

ውይይቱ እስከ ሰኞ ይቀጥላል፡፡ዘገባ የሪፖርተራችን ታአምርአዬሁ ወንድማገኝ ነው፡፡