የአፍሪካን የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና አሰጣጥ ለማጎልበት ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል ተባለ

ጥቅምት 27፤2010

የአፍሪካን የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና አሰጣጥ የበለጠ ለማጎልበት ተጨማሪ ምርምር እንደሚስፈልግ ባለሞያዎች ገለጹ፡፡  

የበሽታውን ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን እና መፍትሄዎቻቸው ላይ የሚመክር መድረክ በሩዋንዳ እየተካሄደ ነው፡፡

አፍሪካዊያንና አለም አቀፍ ተመራማሪዎች  በአለም ጤና ድርጅት  በኩል እ.ኤ.አ. በ2016 በአፍሪካ አህጉር አለም አቀፍ  የኤች አይቨ ኤድስ ህክምና ሽፋን ለሁሉም ለማዳረስ  የተወሰዱ እርምጃዎችን ለመገምገም ነው በኩጋሊ የተሰባሰቡት፡፡

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ስብሰባ  የኤች አይ ቨ ምርመራ እና እንክብካቤ አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ነው፡፡            

ተመራማሪዎቹ   በቀጠናው  ሁሉን አቀፍ የኤች አይ ቪ ኤድስ  ምርመራ እና አንክብካቤ  እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን እና   በዘርፉ የሚደረገውን ምርምር በጋራ ለማጎልበት  በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ በአፍሪካ ሀገሮች ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ በተገቢው መልኩ በማዳረስ ላይ በሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ የተጠናከረ ምርምር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የሩዋንዳ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶክተር ዲኔ ጋሹምባ  አለም አቀፍ ምርመራ እና እንክብካቤ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ እንዲሁም በደማቸው ኤች አይ ቪ/ኤዲስ ያላቸው ሰዎችን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል የበሽታውን ስርጭት ለማስቆም ዋንኛ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ - ሲጂቲኤን