በ2022 የአፍሪካ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ እንደሚሆን ተገለጸ

ጥቅምት 28፤2010

አፍሪካ በአምስት አመት ውስጥ የሞባይል ስልክ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጥፍ በማደግ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሊደርስ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ለዚህ ደግሞ ዘመናዊ ስልኮች እና ፈጣን የኔትዎርክ ዝርጋታዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መገኘታቸው መሆኑን በተደረገ ጥናት ማወቅ የተቻለው፡፡

ተቀማጭነቱን በለንደን በያደረገው ኦቪም የጥናት እና አማካሪ ድርጅት እንደሚገልጸው ከሆነ አሁን  419 ሚሊዮን የነበረው የሞባይል ስልክ ብሮድባንድ ኔትዎርክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በፈረንጆቹ 2022 ከአንድ ቢሊዮን በላይ ይደርሳል፡፡

የዲጂታል ሚዲያ፤ የሞባይል የገንዘብ ዝውውር አገልግሎቶች እና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በአፍሪካ የኢንተርኔት ግንኙነቱ እየሰፋ ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢዎች ከተለመደው አሰራራቸው ተላቀው ወደ ዲጂታል አገልግሎት እንዲሸጋገሩ ጫና እያደረገባቸው መሆኑን ኦቪም የጥናት እና አማካሪ ድርጅት ይገልጻል፡፡

ኤምቲኤን፤ ኦሬንጅና ባሃርቲ ኤርቴል በአፍሪካ ያለውን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ በጀት በመመደብ እየሰሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ምንጭ-ሮይተርስ