የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እየያደገ ነው

ሕዳር 01፣2010

በአፍሪካ የማምረቻ ዘርፍ ማእከል እየሆነች ባለችው ኢትዮጵያ የቻይና ኩባንያዎች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እያሳዩ መምጣታቸው የኢትዮጵያ ኢቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።

ታዋቂው የቻይና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እንደሚያደርግ  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል᎓᎓

ኩባንያው በድሬዳዋ የተቀናጀ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር  ስምምነት ተፈራርሟል ተብሏል᎓᎓

ዥንዋ እንደዘገበው  ከአውሮፓውያኑ 2012 እስከ 2017 በቻይና ኩባንያዎች የተሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ 379 ፕሮጀክቶች ይገኛሉ።

ይህም የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ትልቁን ድርሻ መያዛቸውን ያሳያል ተብሏል።