በአፍሪካ ታዳሽ ኃይል ላይ የሚመክር መድረክ በሞሮኮ ይካሄዳል

ህዳር 01፣2010

በአፍሪካ ታዳሽ ኃይል ላይ የሚመክረው ጉባኤ በሞሮኮ ካሳብላንካ የፊታችን ህዳር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ ከበካይ ጋዝ የፀዳ የሀይል ምንጭ ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡

በውይይቱ ላይ በአህጉሪቱ አረንጓዴ እድገትን ማዕከል ያደረገ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በታዳሽ ሀይልና በመሰረተ ልማት መዋለንዋይ ለማፍሰስ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል ተብሏል፡፡

በታዳሽ ሀይል ፕሮጀክት ግንባታ፣ ገንዘብ በማፈላለግ፣ የአየር ብክለትን የሚከላከሉ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና ፈጠራ የታከለበት ማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ተጨባጭ መፍትሄ በማፈላለግ ዙሪያም በፎረሙ ውይይት እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡    

በፎረሙ ላይ የአፍሪካ ሀገራት የኢነርጂ ሚንስተሮች፣ ስመ ጥር ባለሃብቶች፣ የመንግስታት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እ.ኤ.አ በ2030 የአፍሪካ ታዳሽ ሀይል በአራት እጥፍ ሊያድግ እንደሚችል አለም አቀፉ ታዳሽ ሀይል ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ ሽንዋ