ኬንያዊያን ከፕላስቲክ ተረፈ ምርት ጀልባን በማምረት የአካባቢ ብክለትን እየቀነሱ ነው

ህዳር 02፤2010

ኬንያዊያን ፕላስቲክ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ለመዝናኛ የሚሆኑ ጀልባዎችን በመስራት የአካባቢ ብክለትን እየተከላከሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የሃሳቡ ባለቤት ቤን ሞሪሰን ሲሆን በዚህ የስራ ፈጠራውም በኬንያ የላሙ ባህር ዳርቻዎንና ባህሩን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት እየታደገ ነው፡፡

ይህ ፈጠራው የአካባቢ ብክለትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን የፕላስቲክ ቆሻሻውን ሰብስበው ለሚያመጡም የገቢ ምንጭ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ቤን ሞውሪሰን የፕላስቲክ ተረፈ ምርቱን ለጀልባ መስሪያነት ብቻ ሳይሆን ለአስፋልት መንገድ መስሪያ ግብዓትም እንዲሆን አድርጓል፡፡

ኬንያ የፕላስቲክ ምርት በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ብከለት ለመከላከል ስትል የፕላስቲክ ምርቶች በጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማገዷ የሚታወስ ነው፡፡

ይህ ህግ ጥሶ የሚገኝ አካል የአራት ዓመት እስራት ወይም የ40 ሺህ ዶላር ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ደግሞ የፕላስቲክ ቆሻሻ በባህር ውሃ ላይ የሚያደርሰው ብክለት በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ በፈረንጆቹ 2050 የፕላስቲክ ቆሻሻው ከባህር ዓሳ ቁጥር በላይ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ምንጭ፡ ስካይ ኒውስ