ቡሩንዲ የአለም አቀፉን ፍርድ ቤት ምርመራ አልቀበልም አለች

ህዳር 02፤2010

የአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት አይሲሲ የጦር ወንጀል ፈጽማለች በማለት ምርመራ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ቡሩንዲ አድርጋለች፡፡

የሃገሪቱ የፍትህ ሚኒስትር አይሚ ላውሬንቲን ካኒያን እንደገለጹት ከሆነ ቡሩንዲ ከአለም አቀፉ የዌንጀል ፍርድ ቤት አባልነት እራሷን ያገለለች በመሆኑ ከፍርድ ቤቱ ጋር ተባብራ አትሰራም፡፡

ባለፈው ሃሙስ ፍርድ ቤቱ የጦር ወንጀል ምርመራ በሃገሪቱ ላይ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

የፍርድ ቤቱ ዋንኛ ምክንያትም የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ፕዬር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እወዳደራለሁ በማለታቸው በተነሳ ሁከት ወንጀል ተፈጽሟል የሚል ነው፡፡

 ምንጭ፡ ሮይተርስ