አሜሪካ በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መቆየት እንደሚኖርባት የአገሪቱ ሴናተሮች ገለፁ

ህዳር 3፣2010

አሜሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች ያላትን ቀዳሚ ሚና ለማስቀጠል በፓሪሱ ስምምነት መቆየት እንደሚኖርባት የአገሪቱ ሴናተሮች ገለፁ፡፡

በጀርመን ቦን ከተማ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ምክክር ትኩረቱ የፓሪሱ ስምምነት አተገባበርን መገምገም ላይ ትኩረት አድርጋል።

ከሁለት አመት በፊት የተደረሰው የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት የአለም ሙቀት መጠን አሁን ካለበት የሁለት ዲግሪ ሴልሼስ ጭማሪ ዝቅ እንዲል ማስቻልን ያለመ ነው።

ይህ ግን በድንጋይ ከሰልና በነዳጅ የሚሰሩ ኢንዱስትሪዎችን እንዲበራከቱ የሚፈልጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በሃላ አገራቸው ከስምምነቱ እንደምትወጣ መግለጻቸውን ተከትሎ ስምምነቱ ስለመሳካቱ ብዙዎች ስጋታቸውን እንዲያነሱ ሆነዋል።

ይሁን እንጂ በቦን የአየር ንብረት ለውጥ ምክክር ላይ የተገኙት አምስት የዴሞክራሲ ሴናተሮች አሁንም አሜሪካ ስምምነቱ ውስጥ ናት፥ አለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት በሚያደርገው ርብርብም ቀዳሚ ሚናዋን ትጫወታለች ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።