ብልፅግናን ለማምጣት ለፈጠራ ስራ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

ህዳር 3፣2010

በአለም ላይ ልማትን በማፋጠን ብልፅግናን ለማምጣት ለፈጠራ ስራ ትኩረት በመስጠት ሊሰራ እንደሚገባ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ገለፁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በቬትናም ዳናንግ በተካሄደው 25ተኛው የኢስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አባል ሀገራቱ የፈጠራ ስራ ለጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት መሰረት እንደሆነ ሊያስተዋውቁ ይገባል ብለዋል፡፡

ጂፒንግ በንግግራቸው ሀገራቱ ለኢንቨስትመንት እራሳቸውን ምቹ በማድረግ በዘመናዊ ንግድ ኢኮኖሚያቸውን ሊገነቡ ይገባልም ብለዋል፡፡

ሀገራቱ ሁሉን አቀፍ እድገትን ለማስመዝገብ ህዝባቸውን በፍትሀዊ መንገድ ተጠቃሚ እንዲያደርጉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የጋራ የንግድ መስመሮችን በማጠናከር በአለም ላይ የኢኮኖሚ ሚዛናዊነትን ለማምጣት ሊሰሩ እንደሚገባ መግለጻቸውን  ሮይተርስ ዘግቧል።