በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ከአገሪቱ እንዳይወጣ አሜሪካ ጠየቀች

ህዳር4 ፣ 2010

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ከአገሪቱ  ወታደሮቹን በተያዘው ዓመት ማብቂያ ለማስወጣት የያዘውን እቅድ እንዲያዝም አሜሪካ ጠይቃለች፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት አሜሶም በሶማሊያ ያሰማራውን 1000 የሚጠጋውን ጦሩን እ.ኤ.አ እስከ 2017 መጨረሻ ድረስ ለማስወጣት ወስኖ ነበር፡፡

አሜሶም ውሳኔውን ያስተላለፈው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምንክር ቤት የአገሪቱን የፀጥታ ጉዳይ ለሶማሊያ ጦር ለማስተላለፍ መወሰናቸውን ተከትሎ ነው፡፡

አሜሪካ የጦሩን መውጣት የተቃወመችው አሜሶም ሶማሊያን ለቆ ቢወጣ ፅንፈኛው ቡድን አልሸባብ ሊያንሰራራ ይችላል በሚል ፍራቻ ነው፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሶማሊያ የጦር ሀይል በበቂ ሁኔታ ተጠናክሮ የአሜሶምን ቦታ እንኪረከብ ድረስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አክሎ አስታውቋል፡፡

የአሜሶም ጦር ሶማሊያን ቀስ በቀስ እንደሚለቅና 500 የሚሆኑ ወታደሮች የአገሪቱን የፖሊስ ሀይልን ለመደገፍ እንደሚቆይ የአሜሶም ጦር ዋና አዛዥ ፍራንሲስኮ ማዲዬሮም መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ከኢትዮጵያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከቡሩንዲ፣ ከኬኒያና ከጅቡቲ የተውጣጣው የአሜሶም ሰላም አስከባሪ ጦር በሶማሊያ ለ10 ዓመታት ያክል ቆይቷል፡፡  

የሰላም አስከባሪ ጦሩ መቃዲሾን ከአልሸባብ ነፃ አድርጎ ለማቆየት ቢችልም በሌሎች አካባቢዎች ግን ፅንፈኛው ቡድን አሁንም በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡  

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን