የአውሮፓ እና አፍሪካ መሪዎች ስድተኞችን ለመርዳት ተስማሙ

ህዳር 5፤2010

ከአውሮፓ ህብረት እና አፍሪካ አህጉር የተወጣጡ ሚኒስትሮች አውሮፓ ለመግባት በአስቸጋሪ ሁኔታ ሊቢያ ሆነው የሚጠባበቁ ስድተኞችን በጋራ ለመርዳት ተስማሙ፡፡

ስደተኞችን በተለያዩ የስራ ፕሮጀክቶች ማሰማራት እና የተለያዩ የሀብት መፍጠሪያ ዕድሎችን ማመቻቸት የስምምነቱ ዋነኛ አካል ነው ተብሏል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ የትምህርት ዕድል ለማመቻቸትም ታስቧል፡፡

ከ10 ሺህ በላይ ስደተኞች አውሮፓ ለመግባት በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደሚገኙ ዘገባው ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ሀገራቱ የእነዚህን ስድተኞች የኑሮ ሁኔታ ማመቻቸት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የሊቢያ ስድተኞች መዳረሻ የሆነችው ጣሊያን በዚህ ዓመት ብቻ 115ሺህ ስድተኞችን መቀበሏ ታውቋል፡፡ በዚህ ጉዞ ላይ ደግሞ ሶስት ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

ሀገራቱ በጋራ በሰሩት ተግባር የስደተኞች ቁጥር መቀነሱ ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ