የኬንያ መንግስት የኬኒያ አየር መንገድ እዳን ለማቃለል የነበረውን ድርሻ ከፍ አደረገ

ህዳር 5፤2010

የኬንያ መንግስት የሃገሪቱን አየር መንገድ እዳ ለማቃለል በአየር መንገዱ ውስጥ ያለው ድርሻ ከፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ የተደረገለት የእዳ ቅነሳ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ሲሆን ሌሎች የሀገር ውስጥ አበዳሪዎችም በዚህ የእዳ ቅነሳ ላይ መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡

የኬንያ መንግስት የነበረው ድርሻ 29.8 ሲሆን አሁን ወደ 48.9 ማድረሱን ገልጿል፡፡

የኬኒያ አየር መንገድ  እ.አ.አ. በ2016 ከገባበት የገንዘብ ቀውስ ለመውጣት እና ውጤታማ መሆን እንዲችል የ700 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጎማ ተደርጎለታል፡፡

አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2016 የ251 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶበት ነበር፡፡

ምንጭ-ሮይተርስ