የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን ለ6ተኛ ጊዜ አሸነፈ

ህዳር 06፣2010

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ6ተኛ ተከታታይ ጊዜ የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ክብርን ተቀዳጅቷል፡፡

አየር መንገዱ የአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር ባስቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ልቆ በመገኘቱ ነው ሽልማቱን ያገኘው፡፡

የአፍሪካ የአየር መንገዶች ማህበር ሽልማቱን ለኢትዮጵያ የአየር መንገድ ያበረከተው ከሁለት ቀናት በፊት በኪጋሊ ባደረገው ጉባኤ ነው፡፡

አየር መንገዱ ክብሩን የተቀናጀው አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ባደረገው ጥረት፣ ዓመቱን ትርፋማ ሆኖ ማጠናቀቁ እና በጭነት አገልግሎትና በትብብር ውጤታማ ዓመት በማሳለፉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ  ገብርማሪያም በሽልማቱ መደሰታቸውን በመገልጽ፣ የአፍሪካ መንገስታት የአየር ትራንስፖርትን በማሸሻል ኢቨስትመንትን ሊስቡ እንደሚገባ ገልጽዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ 55 ከተሞች በመብረር የአፍሪካ ትልቁ የትስስር መስመር ከፋች ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡም ስካይ ትራክስ በተባለ የዘርፉ ተቋም በአለም አቀፍ ደረጃ የባለ አራት ኮኮብ ደረጃን ማግኘቱ ይታወሳል፡፡    

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ