አቶ አየልኝ ሙሉዓለም የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

ህዳር 7፤2010

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ አየልኝ ሙሉዓለምን የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾመ፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው አምስተኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፌዴራል የስነ ምግበርና ፀረ ሙስና  ኮሚሽን ኮሚሽነር  አቶ አየልኝ ሙሉአለም ሆነው እንዲሾሙ  የቀረበለትን ጥያቄ  በመመርመር በሙሉ ድምጽ  አጽድቋል፡፡

 አቶ አየልኝ ሙሉአለም ከ1983 ጀምሮ በአማራ ክልል  በመምህርነት፣የክልሉ የምእራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ፣የምእራብ ጎጃምና የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የክልሉ የማረሚያ ቤቶች ጽህፈት ቤት ኮሚሽን ሃላፊ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ እና የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ ሆነው ሰርተዋል፡፡