የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት ሊከበርላቸው እንደሚገባ ተገለጸ

ህዳር 7፤2010

ዜጎች በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው በሰላም የመኖር መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት መሆኑ ተገለጸ፡፡

ዜጎች በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው በሰላም የመኖር መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በላከው መግለጫ ህገ መንግስቱ ለዜጎች የሰጠው  በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የመንቀሳቀስ የመኖር እና  ሀብት የማፍራት መብት እንዲረጋገጥ ሁሉም አካል የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

መንግስትም  ይህን መብት ለማስከበር ህገ መንስታዊ ግዴታውን እንደሚወጣ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡም እነዚህ  የቆዩ የመከባበር የመደጋገፍ እና አብሮ በጋራ የመኖር እሴቶች እንዳይሸረሸሩ  በተለመደው በባለቤትነት መንፈስ ከመንግስት ጎን ቆመው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በተመሳሳይ የልማት የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ ጥቃት በመወሰንዘር የእድገት ጉዞን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎችንም ቸል ሊላቸው እንደማይገባም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

 ምንጭ የመንግስት ኮሙኒኬሽን