በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላምን ለማስፈን የሁሉም ባለድርሻ መሆን እንዳለበት ተገለጸ

ህዳር 07፤2010

በሀገሪቱ በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ለማደረግ የተማሪዎች፤ ወላጆች፤ መምህራንና የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች የጋራ ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ጎልቶ የሚታይባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በውስን ተማሪዎች ሰላማቸውን ሊያጡ እንደማይገባ ተጠቁሟል፡፡