የኡጋንዳ ሴት የፓርላማ አባላት ወንዶች ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዲመረመሩ የሚያስገድድ ፖሊሲ እንዲወጣ ጠየቁ

ህዳር 08፣2010

የኡጋንዳ ሴት የፓርላማ  አባላት ወንዶች  ኤች አይ ቪ ኤድስ   እንዲመረመሩ የሚያስገድድ  ፖሊሲ እንዲወጣ ጠየቁ፡፡

የፓርላማ አባላቱ ወንዶች ለኤች አይ ቨ ኤድስ  ስርጭት  ኃላፊነት ስላለባቸው  መንግስት በግዴታ እንዲመረመሩ የሚያደርግ  ፖሊሲ ማውጣት እንዳለበት  መጠየቃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በኡጋንዳ  ፓርላማ  የኤች አይ ቪ ኤድስ ኮሚቴ ሊቀመንበር  ጁዲዝ  አልዬክ  ለቫይረሱ ስርጭት  አብዛኛዎቹ ወንዶች  ቀዳሚ ኃላፊነት ኃላፊነት ስላለባቸው የተነሳው ጥያቄ ትክክል ነው በማለት  ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ወንዶች  ለቫይረሱ ተጋላጭ ነን በሚል ፍርሃት  ከነፍሰ ጡር ሚስቶቻቸው ጋር ሆስቲታል  በመሄድ መመርመር   እንደማይፈልጉ  ተናግረዋል፡፡  

አሁን ግን በቅድመ ወሊድ ምርመራ ወቅት ወንዶች ከነፍሰ ጡር ሚስቶቻቸው ጋር  እንዲመረመሩ  የሚያስገድድ  ፖሊሲ  በሀገሪቱ ጤና ጠበቃ  መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ሴቶች እና  ወጣት ልጃገረዶች በቫይረሱ  መያዛቸውን ካወቁ በኋላ  የፀረ ለኤች አይ ቪ ኤድስ  መድሃኒት መውሰድ  እንደማይፈልጉ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡  

አለም አቀፉ የኤች አይ ቨ  ኤድስ  መረጃና ትምህርት AVERT ያወጣው መረጃ  እ.ኤ.አ. በ2016 1.4 ሚሊዮን ኡጋንዳዊያን ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ሲሆን 28 ሺህ ደግሞ ከኤድስ ጋር  ተያያዥ በሆኑ  በሽታዎች መሞታቸው አመልክቷል፡፡

ምንጭ ፡- ሲጂቲኤን